GIS, Remote Sensing & Satellite Images –

ነጻ የሳተላይት ምስሎችና ተያያዥ ሶፍትዌሮች

የዛሬ ጽሁፌ ከ10 ዓመት በፊት በግል ጉዳይ ምክንያት የተውኩትንና ዛሬ መልሼ እያነሳሁት ስላለሁት የትምህርት ዘርፍ ይሆናል። ጽሁፉ ስለኔ ሳይሆን እናንተን ሊጠቅም ይችላል ብዬ ስለማምን ነው። እኔ ከተውኩት ብኋላ ያለው ለውጥ የሚገርምና አማላይ ነውና በአጭሩ ላካፍላችሁ።

የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪና ስታፍ በነበርኩበት ግዜ ስፔሻላይዝ ማድረግ ከምፈልጋቸው የትምህርት ዘርፎች መካከል አንዱ GIS እና Remote Sensing ነበር። ያን ግዜ ሬለቫንት የሆኑ ሶፍትዌሮችን ማግኘት የማይታሰብ ነው። አንድም አይገኙም። ቢገኙ እንኳን ሰዉ ለማካፈል ፈቃደኛ አልነበረም። አገርን እንደ አጥንት የሚግጥ፣ “የሚያበላ” ዘርፍ ነበርና። ዛሬ (1) በነጻ የሚለቀቁ ሶፍትዌሮች ለቁጥር የሚታክቱ ናቸው። (2) ሳተላይት ኢሜጅ በዓይነት በዓይነቱ (raw, semi-processed, processed) በነጻ የሚያቀርቡ ድርጅቶች ነፍ ናቸው። (3) Digital Elevation Model በነጻ የሚሰጡ ድርጅቶችም አሉ። (4) Land attributes/features በተመለከተም ዲጂታይዝድ የሆነ መረጃ በነጻ የሚሰጡ አሉ። (5) ሶፍትዌሮችን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል፣ ኢሜጅ እንዴት ፕሮሰስ እንደሚደረግ፣ Digital Elevation Model እንዴት እንደሚዘጋጅ ወዘተ የሚያሳዩ ነጻ መጻህፍትና ማንዋሎችም አሉ። (6) ሌክቸሮችም በነጻ በYouTube፣ በCoursera፣ በMOOC፣ በESRI ወዘተ ይሰጣሉ። ራስን ጠቅሞ አገርን ለመጥቀም፣ በጣም ምቹ ሁኔታዎች ተፈጥረዋል።

እነዚህን በነጻ የቀረቡልንን ግብአቶች ተጠቅመን ምን መስራት እንችላለን? ከብዙ በጥቂቱ ምሳሌዎች እነሆ፣

  •  የከተሞች ፕላን ለማውጣት፣ የከተሞች ስፋት ከግዜ አንጻር ለማነጻጸር፣ በከተሞች ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ነገሮች ጂኦሎኬት ለማድረግ፣ የከተሞችካርታ ለማዘጋጀት ወዘተ ይረዱናል።
  • በገጠር የተፋሰስ ጥናት ለማከናወን፣ ለእርሻ፣ ለደን፣ ለዱር እንስሳ፣ ለመስኖ፣ ለገጠር መንገድ፣ ወዘተ አመቺ የሆኑ ቦታዎችን ለማጥናትና ፕላን ለማዘጋጀት ይረዱናል።
  • የወንዞችን ባህሪ የፍሰት መጠን (discharge)፣ ፒክ ታይም፣ ወዘተ ለማጥናት፣ ለግድብ ስራዎች ምቹ ቦታዎችን ለመምረጥ ወዘተ ይረዱናል።
  • ሌሎች ከማህበራዊ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ እልፍ አእላፍ ነገሮችን ለማጥናትና እቅድ ለማውጣት ይህ ዘርፍ ወሳኝ ነው።

ካለን የህዝብ ብዛት አንጻር ሲታይ፣ በብዙ ነገር ኋላ የቀረን ከመሆናችን አንጻር ሲታይ፣ ገና ምንም ያልተነካና ትልቅ ፖለቴንሺያል ያለው ድንግል ዘርፍ ነው። በግልም ይሁን ተቀጥሮ ለመስራት ገበያ የማያጣ ዘርፍ ነው። እያንዳንዱ መስሪያ ቤት ውስጥ ፕላን የሚያዘጋጅና ገንዘብ ያዥ እንዳለ ሁሉ ወደፊት በዚህ ዘርፍ የተማረ ሰራተኛም በእያንዳንዷ መስሪያ ቤት ሊኖር ግድ ይላል። ”ጂኦግራፊክ ኢንተለጀንስ“ ማለት በተለይ ለእንደኛ ዓይነት ኋላ ቀር አገር በአስተማማኝ የለውጥ ጎዳና ዘላቂነት ባለውና በፍጥነት ለመገስገስ በጣም ወሳኝ ነው። የማይረቡ የዘውጌዎች ትርክት ቪድዮና ኦድዮ እያወረዳችሁ፣ ኦንላይ ለሰአታት ላይቭ ተጎልታችሁ፣ አእምሯችሁን ድንቁርናና ጥላቻ በተሞላ ትርክት ከምትደፈድፉት፣ ገንዘብና ግዜያችሁንም ከምታባክኑ፣ ይህን ዓይነት ጠቃሚ ነገር ብትሞክሩ ለራሳችሁም ለወገንም ትተርፋላችሁ በሚል እሳቤ የማውቀውን ላካፍላችሁ የወደድኩት። ይህ ዓይነት እድል እኔ በጣም በሚያስፈልገኝ ግዜ (ከ10 ዓመት በፊት) አልነበረም። ዛሬ በተለይ ለወጣቱና ለታዳጊው ትውልድ አማራጩ በገፍ ቀርቧል። ራሳችሁን መቀየር ከምትችሉበት አማራጭ አንዱንና ቁልፉን ጠቆምኳችሁ።

ለመነሻ ጠቃሚ መረጃዎች – የኔ ቀዳሚ ምርጫዎች – እንሆ!
1. ነጻ ሶፍትዌር – OSGEO4W. ቀዳሚ ምርጫዬ QGIS ነው። ቀጥሎ GRASS ነው። OSGEO4W ሁለቱን ከሌሎች ጋር አንድ ላይ አቀናጅቶ የሚያቀርብ ነው። በተናጠል ኢንስቶል ከማድረግ አንድ ላይ በማድረግ ግዜና ቦታ ይቆጥባል።
2. ነጻ ሳተላይት ኢሜጅ ለማውረድ – USGS Earth Explorer
3. የመንገድና የመሳሰሉ መረጃዎችን ለማግኘት – OpenMapTiles
4. ነጻ ኮርስ – MOOC
5. ነጻ የሚነበቡ ማንዋሎች – QGIS User Guide

በመጨረሻም ለአንዲት የካርታ ስራ በመቶሺዎችና በሚልዮኖች የሚቆጠር የአገር ሀብት የሚቀራመቱ አገር በቀልና የውጭ “ኮንሳልታንሲዎች” ይችን ጽሁፍ ቢያነቡ እንደሚያኮርፉ ይገመታል።  ለማንኛውም አስተያየታችሁን እዚህ ከታች ወይም በፌስቡክ ገጼ አካፍሉኝ።

ሌሎች ተጨማሪ አማራጮች በዝርዝር

አንዴ ከገባችሁበት ደግሞ ስትጎለጉሉ ሌሎች እዚህ ያልተካተቱ፣ የማውቃቸውና የማላውቃቸው ብዙ አማራጮችን ታገኛላችሁ።

Free GIS & RS Software

OSGEO4W

QGIS

GRASS GIS

SAGA GIS

Sentinel Toolbox

R for Spatial Data Analysis

MapGuide

GeoDa

ILWIS

Free Satellite Images

USGS Earth Explorer

Sentinels Scientific Data Hub

NASA’s Earthdata Search

Earth Observation Link (EOLi)

INPE Image Catalog

JAXA Global ALOS portal

NOAA Data Access Viewer

Landcover.org

VITO Vision

Theia – Land Data Center

UNAVCO SAR Archive Search User Interface.

Lectures or Books

ESRI

Spatial Data Visualisation with R

1 reply

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *