, , , ,

የትግራይ ህዝብ እና የህውሓት ግኑኝነት ነባራዊ ገፅታ

የተለየ አፈና

ቀጥተኛ አፈና

ትግራይ ከሌሎች ክልሎች ለየት የሚያደርገው በህውሓት ቀጥተኛ አፈና ስር መሆኑ ነው። ህውሓት በአገሪቱ የፖለቲካና የኢኮኖሚ የበላይነቱን የተቆናጠጠ ብቸኛ “ሉአላዊ” ድርጅት እንደመሆኑ መጠን፡ ይህን የበላይነቱን ለማስጠበቅ ቁልፍ ቁልፍ የመንግስት ስልጣኖችን በመያዝና ሁሉንም መንግስታዊ መዋቅር በቁጥጥሩ ስር በማድረግ አገሪቱን በእግር ብረት ጠፍሮ እየገዛ እንደሆን ይታወቃል። በሁሉም ክልሎች ተመሳሳይ የሆኑ የጋራ የአፈና ዘዴዎች ተዘርግተዋል። የጸጥታ ሀይሉ፣ መከላከያው፣ የፍትህ ተቋማቱ፣ የደህንነት ክፍሉ ወዘተ በህውሓት ቁጥጥር ስር ውለው የኢኮኖሚና የፖለቲካ የበላይነቱን ለማስጠበቅ የሚጠቀምባቸው የፖለቲካ መሳሪያ መሆናቸው እሙን ነው።

ያም ሆኖ ሌሎች ክልሎች በህውሓት ቀጥተኛ አፈና ስር አይደሉም ያሉት። አፈናው በሌላ third party (ወይም ጠፍጥፎ በሰራቸው ተላላኪ ድርጅቶች) አማካኝነት የሚገለጽ ነው። እነዚህ ፓርቲዎች የህውሓትን ያክል ጥንካሬና aspirations ኖሯቸው ህውሓት በሚያፍነው ወይም ማፈን በሚፈልገው ደረጃ ህዝብን የሚያፍኑ አይደሉም። እንዳውም አንዳንዴ የሚገዳደሩበት (resist የሚያደርጉበት) ሁኔታ አለ። በነዚህ ክልሎች ውስጥ ለሚኖር ህዝብ ይህ ክፍተት ተቃውሞውን በተለያየ መንገድ ለመግለጽ በአንጻራዊነት የተሻለ ዕድል ፈጥሯል። ለምሳሌ የግል ፕሬሶችን በመክፈትና ህዝብን በማነቃቃት፣ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችን በመመስረትና በህጋዊ ተቃዋሚነት በመንቀሳቀስ፣ ብሎም በአደባባይ ተቃውሞን በማነሳሳት ረገድ በሌሎች ክልሎችይህ ክፍተት ጉልህ ሚና ተጫውቷል።

ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ ትግራይ በቀጥታ በነሱ ቁጥጥር ስር መሆኑ እና ደግሞ በዚህ ክልል ተቃውሞ ከተነሳባቸው ለህልውናቸው የመጨረሻ አደገኛ በመሆኑ፣ እነዚህ በሌላ ክልል የሚታዩ የህዝብ የresistance መገለጫዎች ለረዥም ጊዜ በትግራይ እንዳይፈጠሩ ማድረግ ችለዋል። የግል ፕሬስ ትግራይ ውስጥ ከነ አካቴው እንዳይፈጠር አድርገዋል። በሌሎች አካባቢዎች አልፎ አልፎ ብቅ የሚሉ የግል ህትመቶችና መጻህፍቶች የትግራይን ምድር እንዳይረግጡ እገዳ ተጥሎባቸዋል። የግል ሚድያ ለመፍጠር የሞከሩ አንድ ወይም ሁለት ወጣቶችን ገና በለጋነታቸው ሳይበራከቱ ልክ አስገብተዋቸዋል። በትግራይ የሚናገረው ህውሓት ብቻ ነው። የሚደመጠው  ህውሓት ብቻ ነው። ሌላ ድምፅ የለም።

በትግራይ ለረዥም ጊዜ ተቃዋሚ ፓርቲ እንዳይመሰረትና በክልሉ እንዳይንቀሳቀስ ግልጽ በሆነ አፈና አግደውታል። ዓረና ትግራይን ዘግይተውም ቢሆን የፈቀዱት አንድም የመድብለ ፓርቲ ስርዓት በክልሉ እንደተጀመረ ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ለመጠቀም፣ ሁለትም መስራቾቹ የቀድሞ የህውሓት ታጋዮች በመሆናቸው ህዝብ ከኛ በተለየ መልኩ ሊቀበላቸው አይችልምና ለስልጣናችን አደጋ አይሆኑም በሚል እሳቤ መሆኑ ይታወቃል። ያም ሆኖ ሰርጎ ገቦችን ከትተው በየጊዜው ሲያፍረከርኳቸው ይስተዋላል። ስርዓቱን አምርረው የሚቃወሙ ወጣቶች አማራጭ ፓርቲ ሊመሰርቱ ቀርቶ ብሶታቸውን የሚጋሩበት፡ተቃውሞና ትችታቸውን የሚናገሩበት መድረክ ፈጽሞ አያገኙም። የህውሓት ቀይ መስመር በትግራይ ደመቅ ይላል። ህውሓት ተቃውሞ በትግራይ ፈጽሞ አይፈቅድም። እስከመቼውም ድረስ ሊፈቅድ አይችልም።

የመረጃ አማራጭ ከሌለ፣ በክልሉም ሆነ ከክልሉ ውጪ ህውሓት እየሰራቸው ያሉ ወንጀሎች ህዝቡ የሚያውቅበት መንገድ ከሌለው፣ ህዝቡ ለነጻነቱ እንዲቆም በሰላማዊ መንገድ የሚያነሳሱና የሚያስተምሩ ወጣቶችና ፓርቲዎች ከሌሉ፣ በራሱ ጊዜ ህዝብ ተነስቶ ለመቃወም እድሉ ጠባብ ይሆናል። ወይም በጣም ጊዜ የሚጠይቅ ይሆናል። በአንድ በኩል ህዝቡ ከመታፈኑ በተጨማሪ በጥላቻ የተሞሉ ፕሮፓጋንዳዎችን በየቀኑ ሲለፍፉበትና ሲያሴሩበት ስለሚውሉ በፍርሃት እንዲሸበብ  ተደርጓል። በሌላ በኩል ደግሞ በብዙዎች ዘንድ ባልተነቃባቸው ተዘዋዋሪ የአፈና መሳሪዎችን በመጠቀም ህዝቡ በተለይ የገጠሩና የከተማ ድሃው ክፍል ሰጥ ለጥ ብሎ ለህውሓት እንዲገዛ ተደርጓል።

5 replies
  1. Simon
    Simon says:

    እጅግ በጣም ገራሚ ትንተና ነዉ ሶሎሞን ያቀረብከዉ!!! እዉነታዉን ከነ ሙሉ ጭብጦቹ ስላቀረብከዉ በጣም ልትመሰገን ይገባል!!!

    Reply
  2. kedir Seid Mohammed
    kedir Seid Mohammed says:

    እንደኔ እምነት ይህ ጽሁፍ የትግራይ ህዝብ ያለበትን ተጨባጭ በጥልቀት የመረመረ፤ ምናልባትም ስለ ትግራይና ስለ ህዝቧ አስመልክቶ እስካሁን ካነበብናቸው ጽሁፎች በይዘትም በአቀራረብም የተለየ እንደሆነ አምናለው እናም ካለው ነባራዊ ሁኔታ ተነስቼም እውነት የትግራይ ህዝብ ምን ሁኔታ ላይ ነው ያለው፤ ከሌላው ማህበረሰብ ለየት ያለ የስርአቱ ታማኝ ደጋፊ እንዲሆን ያስቻለው፤ ሰጥ ለጥ ብሎ እንዲገዛላቸው ያደረገው እውነት ወዶ በፍቃዱ ነው ወይስ ከማያውቁት መልአክ የሚያውቁት ሰይጣን አይነት ነገር ሆኖበት ነው እናም የመሳሰሉ የብዙ ሰዎች ጥያቄ እዚህ ጽሁፍ ውስጥ መልስ እንደሚገኝባቸው አምናለው። ምናልባትም ያለንን የተሳሳተ እይታ ያስተካክላል ብየ ተስፋ አደርጋለው። ብዙዎቻችን ያለን አመለካከት ላይ ላይ ከሚታዩት አንድአንድ ማኒፈስቴሽኖች የዘለለ በጉዳዩ ላይ ጠለቅ ያለ ግንዛቤ ያለን መስሎ አይሰማኝም።

    መልካም ንባብ ፡)

    Reply

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *