, , , ,

የትግራይ ህዝብ እና የህውሓት ግኑኝነት ነባራዊ ገፅታ

 

ትግራይ የተለየ ተጠቃሚ?

እንግዲህ ከላይ የተዘረዘሩትን የአፈና መሳሪዎች ላነበበ የትግራይ በተለየ ተጠቃሚነት ሊዋጥለት የሚችል አይሆንም። ትግራይ ከሌላው በተለየ ተጠቃሚ አይደለም። እንዳውም በተለየ የታፈነ ህዝብ ነው። ይህ ማለት ግን በተለየ የተጠቀመ ክፍል የለም ማለት አይደለም። በፍጹም። እንዳውም በተገላቢጦሽ በስርዓቱ በተለየ ተጠቃሚ የሆነው ክፍል የወጣው ባብዛኛው ከዚህ ክልል ነው። በቁጥር ጥቂቶች ናቸው ነገር ግን ፍጹም የፖለቲካና የኢኮኖሚ የበላይነቱን ተቆናጠውቷል። ህውሓት ዓይኑን ጨፍኖ ሊያሞኘን እንደሚሞክረው በኢህአዴግ ስር እንዳሉት እንደ ማንኛውም ድርጅቶች እኩል አይደለም። የተለየ ተጠቃሚምና ፍፁም የፖለቲካና የኢኮኖሚ የበላይነትን የተቆናጠጠ ብቸኛው ሉአላዊ ፓርቲ ነው።

ፌቀደም ሲል እንደተጠቀሰው ቁልፍ ቁልፍ የመንግስት ቦታዎችን በቁጥጥሩ ስር አድርጓል። ሁሉንም የመንግስት መዋቅሮችና የገቢ ምንጮችን በቁጥጥሩ ስር አውሏል። መከላከያ፣ ደህንነት፣ ፖሊስ፣ ፍርድ ቤት፣ ምርጫ ቦርድ፣ አየር መንገድ፣ አየር ሀይል፣ ጉምሩክ፣ ናሽኛል ባንክ፣ ሚድያ፣ ት/ት ሚንስቴርና ከፍተኛ የት/ት ተቋማት፣ አስመጪና ላኪ ድርጅቶች፣ ግብር ሰብሳቢ ባለስልጣን፣ ቱሪዝም ኢንዱስትሪ፣ የውጭ ምንዛሪ (ጥቁር ገበያ)፣ የመሬት ንግድ፣ የተፈጥሮ ሃብት፣ ገንዘብ አጠባ (money laundary & illicit financing) ወዘተ በህውሓትና በህውሓት ሰዎች ያልተያዘና ከቁጥጥራቸው ውጪ የሆነ አንድም ዘርፍ የለም። ባጭሩ አገሪቱ የግላቸው ንብረት ሆኗለች። ፓርቲውና ከፍተኛ ካድሬዎች የልዩም ልዩ! ተጠቃሚዎች ናቸው። የነዚህ ሰዎች ልዩ ተጠቃሚነትና የበላይነት፣ ከአጠቃላይ የትግራይ (ህዝብ) የበላይነት ጋር ተምታቶ ሲቀርብ ይታያል። ይህ ስህተት ነው። ሊታረም ይገባል።

5 replies
  1. Simon
    Simon says:

    እጅግ በጣም ገራሚ ትንተና ነዉ ሶሎሞን ያቀረብከዉ!!! እዉነታዉን ከነ ሙሉ ጭብጦቹ ስላቀረብከዉ በጣም ልትመሰገን ይገባል!!!

    Reply
  2. kedir Seid Mohammed
    kedir Seid Mohammed says:

    እንደኔ እምነት ይህ ጽሁፍ የትግራይ ህዝብ ያለበትን ተጨባጭ በጥልቀት የመረመረ፤ ምናልባትም ስለ ትግራይና ስለ ህዝቧ አስመልክቶ እስካሁን ካነበብናቸው ጽሁፎች በይዘትም በአቀራረብም የተለየ እንደሆነ አምናለው እናም ካለው ነባራዊ ሁኔታ ተነስቼም እውነት የትግራይ ህዝብ ምን ሁኔታ ላይ ነው ያለው፤ ከሌላው ማህበረሰብ ለየት ያለ የስርአቱ ታማኝ ደጋፊ እንዲሆን ያስቻለው፤ ሰጥ ለጥ ብሎ እንዲገዛላቸው ያደረገው እውነት ወዶ በፍቃዱ ነው ወይስ ከማያውቁት መልአክ የሚያውቁት ሰይጣን አይነት ነገር ሆኖበት ነው እናም የመሳሰሉ የብዙ ሰዎች ጥያቄ እዚህ ጽሁፍ ውስጥ መልስ እንደሚገኝባቸው አምናለው። ምናልባትም ያለንን የተሳሳተ እይታ ያስተካክላል ብየ ተስፋ አደርጋለው። ብዙዎቻችን ያለን አመለካከት ላይ ላይ ከሚታዩት አንድአንድ ማኒፈስቴሽኖች የዘለለ በጉዳዩ ላይ ጠለቅ ያለ ግንዛቤ ያለን መስሎ አይሰማኝም።

    መልካም ንባብ ፡)

    Reply

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *